Biodiversity Conversation and Ecotourism; and Wildlife Managment and Ecotoursim`` በሚል ትምህርት ፕሮግራም ዙሪያ National Level Curriculum Review ተካሄደ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፣ ግንቦት 21፣2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት`` Biodiversity Conversation and Ecotourism; and Wildlife Managment and Ecotoursim`` በሚል ትምህርት ፕሮግራም ዙሪያ National Level Curriculum Review ተካሄደ።
በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞችን በመገምገም በስያሜ ማስተካከያ እና በተዋሄዱ ፕሮግራሞች ዙሪያ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ የማድረግ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ።
በዚሁ መሠረትም `` Biodiversity Conversation and Ecotourism; Wild Life Management and Ecotourism ``የሚል ትምህርት ፕሮግራምን በሚመለከት የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ለማድረግ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የፕሮግራሞችና የሥርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያና የመድረኩ አስተባባሪ አቶ አድነው ኤርበሎ፣ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ተወካይ ምሁራን ፣ ከኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩትና ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለ ሥልጣን ጽ/ቤት ተወካዮች፣ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከግብርና ኮሌጅ መምህር በላይ ማሩ እና የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዳል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፣ምርምር ፣ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ መንግስት የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ እያደረገ ባለው ጥረት ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለተገኙት ምሑራን ምስጋናቸውን አቅርበው ዩኒቨርሲቲው በሌሎች ጉዳዮችም በቀጣይ ተባብሮ ይሠራል በማለት ገልጸዋል።
በዕለቱም በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር እየተከተለ ያለውን አቅጣጫና አቋም በሚመለከት የትምህርት ሚኒስቴር የፕሮግራሞችና የሥርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያና የመድረኩ አስተባባሪ አቶ አድነው ኤርበሎ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ፕሮግራሞች ዙሪያ ከብዛት ይልቅ በጥራት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን እና በዚሁ መሠረትም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች የማዋሄድ ሥራ መሠራቱንና ይህንኑ አቅጣጫም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲረዱት ተደጋጋሚ ውይይቶች መደረጋቸውን አስረድቷል።
አያይዘውም አቶ አድነው ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን ወደ አንድ ማምጣቱ ጠቀሜታው ሀብትን ለመቆጠብ ከማስቻሉም ባሻገር ከተማሪዎች ዝውውር፣ቅጥርና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ጋርም ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ያስችላል ብሏል።
በሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ዙሪያም መነሻ እንዲሆን ቀደም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ ያላቸውን Biodiversity Conservation and Ecotourism ትምህርት ፕሮግራም ዙሪያ የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት በይዘት ዙሪያ ተገምግሞና የስያሜ ለውጥ ተደርጎ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲወርድ መደረጉ በመድረኩ ላይ የተገለጸ ሲሆን አሁንም በተጨማሪ መታየት አለበት በሚል ከባለ ድርሻ አካላት በቀረበ ጥያቄ መሠረት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ይህንኑ ኃላፊነት በመውሰድ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ስለ መሆኑ ተጠቅሷል።
በተሰጠው አቅጣጫ መሠረትም ቀደም ሲል የስያሜ ማስተካከያና የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ተደርጎ ለዩኒቨርሲቲዎች በተሰራጨው Wildlife Conversation and Ecotourism ፕሮግራም የስያሜ ማስተካከልና የሥርዓተ ትምህርት ክለሳን በሚመለከት ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ መሠረትም የስያሜ ለውጥን አስመልክቶ በአዲስ መልክ ሁለቱም ፕሮግራሞች ወደ Biodiversity and Ecotourism Management በሚል ፕሮግራም ስም እንዲስተካከል አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በይዘት ላይም በተደረገው ግምገማና ንጽጽር መሠረትም ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ ኮርሶችን ወደ አንድ የማምጣት እና የማያስፈልጉትን የማስወጣት ተግባር ስለ መከናወኑ ተጠቅሷል።
በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ተቋማት በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው የነገውን ሀገር ተረካቢ ትውልድ በትምህርት ዘርፍ በተሳካ ሁኔታ ለመቅርጽ እንዲያስችል ላደረጉት ተግባር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም አማራጩና የሚያዋጣው ተባብሮ መሥራቱ ስለ ሆነ በምርምርና በሌሎች ጉዳዮች ተባብሮ ለመሥራት ዩኒቨርሲቲው ፈቃደኛ መሆኑንም በንግግራቸው ውስጥ አካቷል።




















































