የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኮሌጅ የጤና ባለሙያዎች 27ኛዉን የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በበየነ መረብ ተከታተሉ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም (ቡሆዩ)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች በጅማ ከተማ ''ዘላቂ ኢንቨስትመንት እና ኢኖቬሽን ለጠንካራ ጤና ሥርዓት '' በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን 27ኛውን የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በበይነ መረብ በቀጥታ ተከታትሏል።
በከተማዋ የተካሄደዉ ይህ ዓመታዊ ጉባኤ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሆን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ባሉበት ሆነዉ ከጥቅምት 13-14/2018 ለሁለት ቀናት በበይነ መረብ ተከታትሏል ።
ከጉባኤዉ ማዕከል በቀጥታ በበይነ መረብ ለሁለት ቀናት ስተላለፍ የነበረዉን ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባዔን አስመልክተዉ መግለጫ የሰጡት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዋቆ ደደቻ ሲሆኑ ሥልጠናዉ ሀገራችን በጤናው ዘርፍ ያለችበትን ደረጃ ወጥ በሆነ ሁኔታ መረጃ ማግኘት የተቻለበት ከመሆኑም ባሻገር ለቀጣይ ግዜያት በጤናው ዘርፍ ለማሳካት በተነደፉና በተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎች እና መሰል አንኳር ተግባራት ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መጨበጥ የተቻለበት ጉባኤ መሆኑን በመግለፅ በኢንስቲትዩት ደረጃም በበጀት ዓመቱ በጉባዔው የተላለፉትን ውሳኔዎችና መልዕክቶችን በመከተል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚደረግ ተናግሯል።














































