ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከፋነ - አጋ ፋዉንዴሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ህዳር 20/2018 ዓ.ም፡ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ይህ ምሥረታ ወይም ፋዉንዴሽኑ ህዳር 23/2016 ዓ/ም በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን ፤ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ቀደም ሲል 72ኛ የጉጂ አባ ጋዳ በነበሩና የክብር ዶኮቶሬት ተሸላሚ በዩባ አጋ ጤንጤኖ ተጀምሮ የነበረዉን ሪዕይ በማስቀጠል፣ ነባሩን የገዳ ስርዓት ባህላዊ እሴቶቹን ሳይለቅ እንዲጠናከር መስራት፤ የባህል ማዕከላትን ማደራጀት የመሳሰሉ ተግባራትን ማከናወን ሲሆን የታለመለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ደግሞ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የገዳ እና ባህል ጥናት እንስቲትዩት ጋር በአጋርነትና በትብብር በገዳ ስርዓት ዙሪያ አብሮ ለመስራት ይህ የመግባቢያ ሠነድ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተፈርሟል።
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ በጉጂ ኦሮሞዎችና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች ሳይበረዝና ሳይሸራረፍ በነባሩ የገዳ ሥረዓት ዙሪያ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣የሀገር በቀል እዉቀትና ጥበብ ለትዉልድ እንዲሸጋገር ማድረግ ፣ የገዳ ስርዓት እሴቶች በመንግስት አስተዳደር ሥረዓት ውስጥ ጎን ለጎን ሚናቸዉን እንዲጫወቱ ማድረግ ናቸዉ፡፡
በዕለቱ የመግባቢያ ሠነዱን የፈረሙት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እና ፋነ አጋ ፋዉንዴሽን መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ሀይሌ ገብሬን በመወከል የመግባቢያ ሠነዱን የፈረሙት እጩ ዶ/ር ጋልቹ ጃርሶ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም ለሠነዱ ትግበራና ለዉጤታማነት ሁለቱም ፈራሚ ወገኖች አብሮ በመተባበር የዓላማዉን ዋና ሀሳብ ወደፍት ማሰጓዝ ና ማራመድ እንደሚገባቸዉ ሁለቱም አካላት በመስማማት የፊርማዉ ሥነ ሥረዓት ተጠናቋል ።














































