Statistical Package for the Social Sciences (SPSS) and AMOS ›› በሚል ርዕስ ለመምህራን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም (BHU)
ሥልጠናዉ የተዘጋጀዉ በብዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አስተባባሪነት ሲሆን ከተለያዩ የኮሌጁ ትምህርት ክፍሎች የተወጣጡ መምህራንና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በተቋሙ እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎች ተሳታፊ ስለመሆናቸዉ ተገልጾዋል፡፡
በቦታው ላይ በመገኘት ስልጠናውን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት የብዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መ/ር ማንዶ ገናሌ ሲሆኑ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትኩረት ተሰጥቶኣቸው እየተከናወኑ ካሉት ተግባራት አንዱ በዋናነት የጥናትና ምርምር ሥራዎች መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን የምርምር ሥራዎች በተሻሻሉ ሶፍትዌሮች በመደገፍ ጥራት ያላቸዉን የጥናትና ምርምር ሥራዎችን መምህራን እንዲሰሩ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሆኑን በንግግራቸው አመላክቷል፡፡

Research Methodology in Social Science: Quantitative and Qualitative research ``በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም (BHU)
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ መምህራን ችግር ፈቺና ወቅታዊ የሆኑ የምርምር ሥራዎችን መሥራት ይችሉ ዘንድ ታሳብ ያደረገ በስነ-ሰብና ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባርነት በኮሌጁ ስር ካሉት የተለያዩ ኮሌጆች ለተመለመሉ መምህራን ለተከታታይ ሦስት ቀናት ተሰጥቷል፡፡

Basic Training on Technology Transfer through Power World Simulator and ETAP soft wares for enhancing the Capacity of Lab assistant and Post Graduate Students``በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ‹‹Basic Training on Technology Transfer through Power World Simulator and ETAP soft wares for enhancing the Capacity of Lab assistant and Post Graduate Students``በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናዉ የተዘጋጀዉ በኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ስር ከሚገኙት የትምህርት ክፍሎች አንዱ በሆነው በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ የትምህርት ክፍል አስተባባሪነት ሲሆን በትምህርት ክፍሉ ሥር ያሉትን መምህራን አቅማቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለማሳደግና ለማብቃት ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑ በስልጠናው ወቅት ተገልጿል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ YOLK ከተባለው ግብረሰነይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ ዋመና ወረዳ በጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  በፀሐይ ሃይል የሚሠራ የሶላር ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አስጀመረ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (BHU)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለ ከደቡብ ኮሪያ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን በሀምበላ ዋመና ወረዳ የኤሌክትርክ ኃይል ካልተዳረሰባቸው ት/ቤቶች አንዱ በሆነዉ ጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ሶላር ዲሽ በመግጠም ትምህርት ቤቱንና ማህብረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የግብረሰናይ ሥራን ለመሥራት ‹‹SOLAR COW››የሚል መጠሪያ ካለው ሌላ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
የሶላር ኃይል ማመንጫው ሊገሳ ዋናው ዓላማ የተማሪዎችን መጠነ ብክነት ለመቀነስ፣የአከባቢው ማህበረሰቡና ቤተሰቦቻቸው በማታ የመብራት ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ሆኖ በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትንም ለመደገፍና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነዉ።

Pages