የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በe-SHE ዙሪያ ለተማሪዎቹ ገለፃ አደረገ፡፡

ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታን በኦንላይን ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ ስለመሆኑ የተነገረለት e-SHE (e-learning for strengthening higher education) ባለፈው የትምህርት ዘመን የሬሜዲያል ትምህርታቸውን ተከታትለው በ2017 የትምህርት ዘመን ለአንደኛ ዓመት ለተመዘገቡ ተማሪዎችና ከ2ኛ ዓመት በላይ ላሉት መደበኛ ተማሪዎች በአይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ በኩል ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ገለፃዉን ያደረጉት የአይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድማገኝ ሸበራ ሲሆኑ ኮርሱን ወስደው ለጨረሱ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑንና በፈተናዉም ከ80% በላይ ማምጣት የሚጠበቅ ስለመሆኑም ተናግሯል፡፡

e_Learning for Strenthening Higher Education(e-SHE)

ጥቅምት 08/2017

ትምህርት ሚኒስቴር e_Learning for Strenthening Higher Education(e-SHE) የተሰኘ ፕሮግራም በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲተገበር እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህም ፕሮግራም የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚያችል ከመሆኑ እንጻር የዩኒቨርሲቲዎች የእቅድ አካል ተደርጎ ሊተገበር እንደሚገባም ጭምር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በዚህም መሠረት በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲም ከት/ሚ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት ይህንንኑ የኤሌክተሮኒክስ ትምህርት ትግበራ ለማስረፅ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ የቆዩና በመሰራት ላይም ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸዉን አጠናቀዉ ወደ ዩኒቨርሲቲያቸዉ ሲመለሱ የመጀመሪያዉን ሳምንት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት Student Success suit(sss) እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ(BHU) ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም

ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረዉን ብሄራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲዉ ሠራተኞች፤የተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ለአቅም ግንባታ ሥልጠና ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ማዕከል የገቡ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጭምር በተገኙበት ሰንደቅዓላማዉ ብሔራዊ ክብርን በጠበቀ መልኩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ፤መዝሙር ተጅቦ እንዲሠቀል የተደረገ ሲሆን በሰንደቅዓላማው ቀን ላይ የተሳተፉ አካላት ቃለ መሃላ በመግባት ወይም በመፈጸም ሥነሥረዓቱ ተጠናቋል ፡፡

Pages